የግብፅ ዕጩ ፕሬዚዳንት ኤል-ሲሲ መነጋገር ይፈልጋሉ

“የአባይ ውኃ ለግብፅ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው” ሲሉ የግብፅ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩና የቀድሞው የጦር ኃይሎቿ አዛዥ አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ ተናግረው ከኢትዮጵያ ጋር ግን በመግባባት መሥራት እንደሚያስፈልግ በሁለት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ በተላለፈ ቃለ-ምልልሳቸው ገልፀዋል፡፡

አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ደግሞ የኤል-ሲሲ ንግግር ከቀድሞዎቹ መሪዎች የተለየ ሆኖ እንዳላገኙት ገልፀው ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡና ያሉትን በተግባር ከፈፀሙ “ከግማሽ መንገድ በላይ ሄደን እንቀበላቸዋለን” ሲሉ ለቪኦኤ ማምሻውን አመልክተዋል፡፡ 

አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ - በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር


ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ሳይሆኑ አይቀሩም እየተባለ በስፋት የሚወራላቸው አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ ካሳወቁ ወዲህ የመጀሪያውን የቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ ላሚስ ኤል ሃዲዲ፣ እንዲሁም ኢብራሂም ኢሣ ከሚባሉ ጋዜጠኞች ጋር አድርገዋል፡፡

ኤል-ሲሲ ሲቢሲ ከሚባለው የግል ቴሌቪዥን ጣቢያና በተመሣሣይ ጊዜም ኦን-ቲቪ በሚባል ሌላ ጣቢያ በተሠራጨው ረዥም ቃለምልልሳቸው የተነተኑት የመጭ ፖሊሲያቸው ንድፍ የሚመስል ሃሣባቸውን ነው፡፡


የአባይ ወንዝ፣ የኅዳሴ ግድብና ከኢትዮጵያ ጋር ያሉ ግንኙነቶች ጉዳዮችም ተነስተዋል፡፡

Read More
Be the first to comment

Related Articles

  • Ethiopia  exports coffee beans
    Ethiopia exports coffee beans
    In Addis Ababa’s affluent Bole neighbourhood, the traditional smell of roasting coffee beans wafts through a thoroughly...
  • List of top television networks in Ethiopia
    List of top television networks in Ethiopia
    የቴሌቪዥን ቻናሎች ★ኢትዮጵያዊ/ሀገር ውስጥ / ☞Kana Tv (12226 H 27500)ው☞ EBS (11595 v 27500)☞ Nahoo (11595 v 27500)☞ Jtv Ethiopia (11595 v...
  • ውቢት ኢትዮጵያ!
    የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን “የ13 ወር ፀጋ” በሚል ርዕስ ከሚያሳትማቸው ፖስተሮች የዝነኛዋ “ውቢት ኢትዮጵያ” አስደናቂ ተፈጥሮአዊ ውበትና ግርማ ሞገስ የታየበት...
  • List of Ethiopian Television Channels
    The mass media inEthiopiaconsist ofradio,televisionand theInternet, which remain under the control of the Ethiopian government,...
  • The New Era of EphremTube is Here | 2026
    The New Era of EphremTube is Here | 2026
    Dear Fans, Today, we are taking a massive leap forward. It has been a long journey, and we are incredibly excited to welcome...

Latest Articles

Most Popular