Most Popular Articles

  • የወሎ ‹‹ላሊበላ›› ትንሣኤ

    በጥቂቱም ቢሆን ዕድሜ እየተጫጫናቸው መምጣቱ ከፊታቸውና ከመላ ሰውነታቸው ይነበባል፡፡ በተለይም ጣታቸው፣ እጃቸው፣ ክንዳቸውና ቀሪ ሰውነታቸው ጠንከርከር የሚለው መድረክ ላይ ወጥተው ማሲንቋቸውን ሲይዙ ነው፡፡

    የ72 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ የሆኑት አቶ አራጌ ኢማሙ በወሎ ላሊበላ የባህል ቡድን ውስጥ ማሲንቆ ተጫዋች ሲሆኑ ከ23 ዓመታት በፊት የፈረሰው የቀድሞው ወሎ ላሊበላ ኪነት ቡድን ውስጥም ሙዚቀኛ ነበሩ፡፡

    አቶ አራጌ እንደሚናገሩት በ1960ዎቹ ‹‹የወሎ የሀገር ባህል ተጫዋቾች ክበብ›› በሚል የተመሠረተው ቡድን 97 አባላት ነበሩት፡፡ ‹‹መሬት ላራሹ›› ከታወጀ በኋላ የቡድኑ አባላት ወደ እርሻና ወደ ሌላም ሥራ ተሰማርተው ይበተኑና የአባላቱ ቁጥር ይቀንሳል፡፡ የቀሩት አባላት በቀለመወርቅ ደበበ ሥር ሆነው ወሎ ላሊበላ የኪነት ቡድን በሚል መንቀሳቀስ ይጀምራሉ፡፡

    የወሎ ላሊበላ ኪነት ቡድን በተነሳ ቁጥር ከአፍ የማትነጠለው ማሪቱ ለገሠን ጨምሮ ዝነኛዋ ዚነት ሙሀባ፣ ወርቅነሽ ተጫን፣ ፀሐይ አበራ፣ ዙሪያሽ አብዩ፣ ፀሐይ ካሳ፣ መሀመድ ይመርና ትግስት አባተጫን የመሳሰሉ የቡድኑ አባላትን በርካቶች ዛሬ ድረስ ያስታውሳሉ፡፡ የቡድኑ የቀድሞም የአሁንም አባል አቶ አራጌ ከማሲንቆ በተጨማሪ አኮርዲዮን መጫወትና ማንጎራጎር የሚሞክሩ ሲሆን፣ የያኔው የኪነቱ አባላት ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ አንስተው ያገኙት የነበረውን አነስተኛ ገንዘብ ሲያስታውሱ ይገረማሉ፡፡

    በርካታ አስተያየት ሰጪዎች በወቅቱ ጥራቱን የጠበቀ ዜማ፣ ግጥሙ ያማረና ባህልን ጠንቅቆ የተከተለ ሥራ የወሎ ላሊበላ ኪነት ቡድን ይሠራ እንደነበር ያወሳሉ፡፡ በሐሳቡ የሚስማሙት አቶ አራጌ በተለይ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ‹‹ፈጣኑ ባቡሩ›› እና ሌሎች በርካታ ተወዳጅ ዜማዎች እንደነበሯቸው ይናገራሉ፡፡ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ‹‹ፈጣኑ ባቡሩን›› ተጫውተው በወቅቱ ከደርግ ሊቀመንበር ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም መጓጓዣ መኪና ማግኘታቸውን ያወሳሉ፡፡

    ወሎ ላሊበላ የኪነት ቡድን ከተበታተነ በኋላ የአብዛኞቹ ዕጣ ፈንታ እንደሆነው ሁሉ ራሳቸውን ለማስተዳደርና ቤተሰብ ለመደጎም በተለያየ አገር እየተዘዋወሩ ማሲንቆ ይጫወቱ ነበር፡፡ ዛሬ ባለትዳርና የስድስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ አራጌ ሙዚቃ በጀመሩበት ወቅት ሙያው ባይከበርም ለሙያው ያደረጉትን ጥረት ይናገራሉ፡፡ 

    ከቡድኑ ወጥተው ከገጠማቸው ውስጥ ያጫወቱን፣ በአንድ ወቅት ባለቤታቸው የነበሩት ሴት ልጅ ወልደው ይሞትባቸዋል፡፡ ልጁ ሲሞት የባለቤታቸው ቤተሰቦች ‹‹የላሊበላ ልጅ ምን ያደርግልሻል›› እያሉ ያጥላሏቸው ነበር፤ በዚህ የተነሳ ለፍቺ እንደተዳረጉም ይናገራሉ፡፡

    ‹‹በሙያው ስንናቅበት ኖረናል›› የሚሉት ሙዚቀኛው ዛሬ ላይ የተሻለ አመለካከት አለ ብለው ስለሚያምኑ ዳግም የወሎ ላሊበላ ቡድን አባል መሆናቸውን በበጎ ያዩታል፡፡ አቶ አራጌ የያኔው ቡድን ላይ የሚደርስ የለም ቢሉም፣ ምንም ቢሆን ደግሞ መሰባሰቡና የሙዚቃ ሕይወትን በኅብረት መግፋቱ መልካም ነው ባይ ናቸው፡፡ በቡድኑ ዳግም ዕድል ያገኙት ባለሙያው ሕይወቴ እስካለ ድረስ በቡድኑ ውስጥ እኖራለሁ ይላሉ፡፡

    ዛሬ ላይ ሆነው ወደ ኋላ ሃያ ሦስት ዓመታትን አሻግረው ሲመለከቱ፣ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ደማቅ አሻራ አሳርፎ፣ ተተኪን አፍርቶ ለመዝለቅ ይንደረደር የነበረው ታላቁ የወሎ ላሊበላ ኪነት ቡድን መበተኑን በርካቶች በቁጭት ይናገራሉ፡፡ 

    የወሎ ላሊበላ ኪነት ቡድን በደርግ ወቅት በተበረከተላቸው መኪና በመንቀሳቀስ የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ በተሰጣቸው ኃላፊነት በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረዋል፡፡ አገራዊ መልዕክት ካሏቸው ሙዚቃዎች በተጨማሪ ልዩ ልዩ ቅኔያዊ ትርጓሜ ያላቸው ሥራዎች ካበረከቱት የቡድኑ አባላት አንዳንዶቹ ጥላሁን ገሠሠና መሀሙድ አሕመድን የመሰሉ ሙዚቀኞች የነበሩበት የሕዝብ ለሕዝብ ቡድን አባላትም ነበሩ፡፡

    በርካታ ድምፃውያን፣ ተወዛዋዦችና የባህል ሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾች ያፈራው ይህ ቡድን ኢሕአዴግ ሲገባ አባላቱ ተበታትነው ገሚሱ በሙዚቃ ሕይወታቸው ሲቀጥሉ ቀሪው ወደ ሌላ ሕይወት ፊታቸውን አዙረዋል፡፡ የቡድኑ መፍረስ ዘወትር ይቆረቁራቸው የነበሩ አባላቱ በተለይም ቀድሞ በቡድኑ ከበሮ ተጫዋች የነበረው ዳምጤ መኰንን (ባቢ) ከረዥም ጊዜ ጥረት በኋላ በምሥራቅ አማራ ያሉ ወጣቶችን መልምለውና ከቀድሞ ቡድን ጥቂት አባላት አክለው ዳግም በኅብረት እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡

    ይህ የወሎ ላሊበላ የባህል ቡድን በአዲስ አወቃቀር ከተቋቋመ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ የተመለመሉት ወጣቶች ለስድስት ወር ያህል በወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮምቦልቻ ካምፓስ ውስጥ ሥልጠና ከተሰጣቸው በኋላ መስከረም 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ቡድኑ በይፋ ተመርቆ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ ቡድኑ ደሴ ውስጥ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ በተለያዩ አገሮች እየተዘዋወረ ሙዚቃና ውዝዋዜ አጣምሮ ያቀርባል፡፡ ቡድኑ ባለፈው ጥር ወር በተካሄደው 4ኛው የባህል ፌስቲቫል ላይ ክልሉን ወክሎም ቀርቦ ነበር፡፡ 

    ከዓመታት በኋላ ዳግም የተነሳው ቡድኑ ድምፃውያን፣ ባህላዊ ሙዚቃ  መሣሪያ ተጫዋቾችና ተወዛዋዦችን አጣምሮ 34 አባላት የያዘ ሲሆን፣ በርከት ያሉ ብሔር ብሔረሰቦችን ሙዚቃ ከልዩ ልዩ ባህላዊ መገለጫዎች ጋር ያቀርባል፡፡

    በአማራ ልማት ማኅበር በተገነባ ማዕከል መድረክ ላይ ያየናቸው የቡድኑ አባላት አንድ ብሔረሰብን ከሚገልጽ አልባሳት ወደ ሌላው ቀይረው በአዲስ ኃይል ወደ መድረኩ ለመመለስ የሚወስድባቸው ጊዜ አጭር ነው፡፡ ለአንድ ምሽት የሚያቀርቧቸውን ብሔረሰቦች ውዝዋዜ ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን መገለጫ ባህል በአጫጭር ሙዚቃዊ ተውኔቶች ለማሳየት ይሞክራሉ፡፡ 

    ከወጣቶቹ አንዱ ሀብታሙ መሀመድ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ውዝዋዜ ወቅት ፊቱ ላይ ለተወዛዋዥነት ያለውን ፍቅር ማንበብ ይቻላል፡፡ ከአንድ እንቅስቃሴ ወደሌላ እንቅስቃሴ በተዘዋወረ ቁጥር ለሙያው ካለው ፍቅር አሻግሮ ችሎታውን መመልከት ይቻላል፡፡

    ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሐይቅ የተወለደው ሀብታሙ የ22 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት የመሰናዶ ትምህርቱን እየተከታተለ በነበረበት ወቅት የኪነት ቡድን አባል መሆን ለሚሹ የተደረገ መጥሪያ ይሰማል፡፡ ልጅ ሳለ አንስቶ ወደ ሙዚቃው ዓለም መቀላቀል ምኞቱ ነበረና ሳያመነታ ጥሪውን ተቀብሎ ተወዳደረ፡፡

    ውድድሩን አልፎ በሥልጠናው ወቅት በየወሩ መገምገሚያ ፈተና የነበረ ሲሆን፣ ከመጀመሪያው አንስቶ የነበሩትን ዙሮች አልፎ የመጨረሻው ዙር ውስጥ የቡድኑ አባል ከሆኑት ተወዛዋዦች መካከል ተቀላቅሏል፡፡ ሀብታሙ ባህላዊ ውዝዋዜ ሲያቀርብ ሐሴት ቢሰማውም ‹‹የተፈጠርኩበት ወሎን ያህል የምወደው ጭፈራ የለም፤›› ይላል፡፡

    ሀብታሙ ዛሬ የወሎ ላሊበላ የባህል ቡድን ዳግም መቆርቆር ምክንያት በየዕለቱ በሚወደው ሙያው ውስጥ እንደሚኖር በሀሴት ተሞልቶ ይናገራል፡፡ የታሪካዊው ባህላዊ ቡድን አባል ከመሆን ባሻገር በሙያው የረዥም ዓመታት ዝናን ካተረፉ ባለሙያዎች ጎን መሥራቱና በየዕለቱ የውዝዋዜ ችሎታውን ለማሳደግ ዕድል ማግኘቱ ያስደስተዋል፡፡ የቡድን አጋሮቹ እርስ በርስ ልምድ ከመለዋወጥና ከመተራረም በዘለለ በፍቅር የሚሠሩ መሆኑ ሙያዊ ሕይወቱን ቀና እንዳደረገለትም ይናገራል፡፡

    ወጣቱ ወሎ ላሊበላ የባህል ቡድን በአካባቢው ባሉ ሰዎች የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ባህል ከማስተዋወቁም በላይ የቀድሞውን ባህላዊ ቡድን ሕይወት የዘራበትና ደሴን በማስተዋወቅ ረገድ በበጎ እንደሚያነሳቸውም ይናገራል፡፡

    ከአንድ ድምፃዊ ጓደኛው ጋር የሚኖረው ሀብታሙ የባህል ቡድኑ በተለያዩ ቦታዎች የሚደረግለት ጥሪ ያስደስተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ወደ ጎንደርና ሌሎች አገሮች በመሄድ ያቀረቡትን ዝግጅት በትውስታ የሚያወሳው ሀብታሙ በውዝዋዜ ዝነኛ የሆኑትን እያጣቀሰ ነገ እነሱ የደረሱበት የመድረስ ህልሙን አስረግጦ ይናገራል፡፡

    ሌላው ወጣት ሀዲሴ ገብረማርያም በአዲስ አበባ እምብርት አራት ኪሎ የተወለደ ሲሆን፣ ቡድኑን በባህል ውዝዋዜ ሥልጠና ለማገዝ በሚል ከዓመት በፊት ወደ ደሴ ያቀናል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ የባህል ቤቶች ተወዛዋዥ የነበረው ሀዲሴ የወሎ ላሊበላ ቡድን አባላትን ከተመለከተ በኋላ ጓዙን ጠቅልሎ አዲስ አበባን ተሰናብቶ ደሴ ላይ ከትሟል፡፡ ‹‹አዲስ አበባ ብትናፍቀኝም፤ የወሎ ላሊበላ ባህል ቡድን ፍቅራቸው አሸንፎኛል፤›› የሚለው ሀዲሴ ቡድኑ እንቅስቃሴ የጀመረ ሰሞን አዲስ አበባ መጥተው ለምክር ቤት ያቀረቡትን ዝግጅት ያስታውሳል፡፡

    በባህል ማዕከሉ ውስጥ የሚስረቀረቅ ዜማ ካቀረቡት አንዷ ዓለም ውቤ በወሎ ላሊበላ የባህል ቡድን ውስጥ ድምፃዊት ናት፡፡ በተወለደችበት አካባቢ የነበረ የገበሬ ማኅበር ኪነት አባል ከመሆን ተነስታ የዚነት ሙሀባን ዘፈኖች ዳግም ተጫውታ አልበም አውጥታለች፡፡ ልጅ እያለች ‹‹መቅደላ›› በተሰኘ የኪነት ቡድን በነበረችበት ወቅት ከወሎ ላሊበላ የኪነት ቡድን ጋር ሙዚቃ እየተዋዋሱ ይጫወቱ ነበር፡፡

    የቀድሞ ወሎ ላሊበላ ቡድን ከፈረሰ በኋላ እሷም ከነበረችበት ቡድን የወጣችው ዓለም፣ ቡድኑ ዳግም በመነሳቱ ደስተኛ መሆኗን ትናገራለች፡፡ በተለይም የወሎን ባህል ከዚያም በላይ የኢትዮጵያን ባህል የማስተዋወቅ ፍላጎት ያላት ዓለም ከቀደሙት ድምፃውያን የማሪቱ ለገሰንና የዚነት ሙሀባን ፈለግ ተከትሎ አልበሞች የማሳተም ህልም አላት፡፡

    ‹‹ሙዚቃ በመዋዋስ የማውቀው ቡድን ዛሬ ጠቅልዬ ገብቻለሁ በምንም የምላቀቅ አይመስለኝም፤›› የምትለው ዓለም፣ በወሎ ላሊበላ የባህል ቡድን የቀድሞው ፍቅርና መተሳሰብን ዛሬ ማግኝቷ ዋጋ የማይከፈልበት መሆኑን ትናገራለች፡፡

    ስለ ባህል ቡድኑ አስተያየታቸውን ከሰጡን ሌላው በኮካ ኮላ ሱፐር ስታርስ ውድድር ላይ ያለፈውን ዙር በአሸናፊነት ያጠናቀቀው ታደሰ መኰንን  ነው፡፡ በደርግ ወቅት በነበረው ወታደራዊ ክፍል ሙዚቃዊ እንቅስቃሴውን አጠናቆ ወደ አዲስ አበባ፣ በመቀጠልም ወደ ደሴ ተመልሶ ኑሮውንና የሙዚቃ ሕይወቱን በትውልድ አገሩ አድርጓል፡፡

    በቡድኑ በሙዚቀኝነት እንዲሁም በድምፅ በማሠልጠን የሚገኘው ታደሰ እሱ ብቻ ሳይሆን በርካቶች ቡድኑ ከፈረሰ በኋላ ያስቆጫቸው ነበርና የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወደ ተሻለ ደረጃ የማድረስ አቅም የነበረው ባህላዊ ቡድን ለመመለስ ከሙያዊ አጋሮቹ ጋር ጥናት አካሂዷል፡፡

    ታደሰ የባህል ቡድኑ ዳግም መቋቋሙ ተቀዛቅዞ የነበረውን የሙዚቃ መንፈስ የሚያነቃቃ፣ ቱባ ባህል የሚያስተዋውቅ፣ ለአገሪቱ የሚሆኑ ሙዚቀኞችን የሚያፈራ፣ ኅብረተሰቡን የሚያነቃቃ፣ የቱሪዝም ዕድገቱን የሚያነሳሳ ነው ይላል፡፡

    ከምሥራቅ አማራ የተወጣጡ ቢሆንም መላው ኢትዮጵያን የሚወክል ቡድን እንደሆነ የሚናገረው ታደሰ፣ ከሚኖሩበት ማኅበረሰብ አልፎ በመላው ዓለም የኢትዮጵያን ባህል አስተዋዋቂ እንደሚሆኑ ያለውን እምነት ይናገራል፡፡ በዕድሜ የገፉት ለተተኪ የሚሆን ዕውቀት እያስተላለፉ እንዲሁም ወጣት አባላቶች በጥቅም ሳይደለሉ በጥንካሬ የሚንቀሳቀሱበት እንጂ እንደቀድሞው በድንገት ያለምትክ የሚፈርስ እንደማይሆን ያለውን ተስፋም ይናገራል፡፡

    የቡድኑን አባላት የመለመለው፣ የቡድኑ አሠልጣኝ እንዲሁም የቀድሞው ወሎ ላሊበላ ኪነት ቡድን አባል ዳምጤ እንደሚገልጸው ከደብረብርሃን እስከ ሰቆጣ ባለው አካባቢ የሚገኙ ወጣቶች የቀድሞን የኪነት ቡድን ታሳቢ በማድረግ ተሰባስበዋል፡፡

    Read More
    Read more
  • Tenorshare iPad Data Recovery [ iPad 4, Mini, 3, 2 ]

    Tenorshare iPad Data Recoveryis a professional iPad data rescue tool for iPad. This software provides 3 modes to retrieve lost iPad photos, contacts, notes, memos, SMS message, Contacts, Call History, Photos, Voice Memos, Reminders, SMS attachments, Safari bookmarks, Whatsapp data(message, photo, video), Tango and other 16 types of files without iTunes backup files. You can also restore lost data from iCloud backup. It will never overwrite the existing data on your iPad.

    Read More:

    Read more
  • Will Ethiopia's Grand Renaissance Dam dry the Nile in Egypt?

    Ethiopia is pressing ahead with construction of a major new dam on the River Nile, despite stiff opposition from Egypt. BBC correspondents in both countries report from both sides of an increasingly bitter water dispute.

    Emmanuel Igunza, Ethiopia

    A vast section of northern Ethiopia has been turned into a giant building site.

    Construction of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (known as Gerd) is now about 30% complete.

    The whole project spans an area of 1,800 sq km (695 sq miles).

    Once completed, in three years, it will be Africa's largest hydropower dam, standing some 170m (558ft) tall.

    At a cost of $4.7bn (£2.9bn) it will also be hugely expensive - mostly funded by Ethiopian bonds and taxpayers.

    The dam is located in the Benishangul region, a vast, arid land on the border with Sudan, some 900km north-west of the capital Addis Ababa,

    Temperatures here can get as high as 48C (118F). Most of the vegetation that existed on the dam site has been cleared to make way for the construction, and the area is now extremely dusty.

    In May last year, the builders achieved their first milestone when they diverted the course of the Blue Nile. 

    Read More
    Read more
  • List of Ethiopian Television Channels

    The mass media in Ethiopia consist of radio, television and the Internet, which remain under the control of the Ethiopian government, as well as private newspapers and magazines. In comparison to the length of Ethiopia's over-2,000-year history as a sovereign nation, the media is a very recent phenomenon.

     

    List of Television Channels

    Read more
  • Daniel Kibret-ዝኆኑም ትንኙም

    አንበሳ በሚገዛው አንድ ጫካ ውስጥ አያሌ እንስሳት ይኖሩ ነበር፡፡ አንድ ቀን አንበሳ ለአንድ የሥራ ጉዳይ ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ ተነሣ፡፡ የእርሱ መሄድ በእንስሳቱ ዘንድ በተሰማ ጊዜ የጫካውን ሕልውና በተመለከተ ጥያቄ ተነሣ፡፡ ጦሩን ማን ይመራል? ገንዘብ ማን ይይዛል? ምግብ ማን ያከፋፍላል? መልእክት ማን ይቀበላል? ዳኝነት ማን ይሰጣል? ሠራተኛ ማን ያሠማራል? ሹመት ማን ይሰጣል? እያሉ እንስሳቱ መጠያየቅ ጀመሩ፡፡ በዚያ ጊዜ አንበሳ ሁሉንም ነገር ጠቅልሎ ይዞት ስለነበር አሁን እርሱ ሲሄድ ነገር ዓለሙ ሁሉ ሊዛባ ደረሰ፡፡
    አንበሳ ችግሩን ቢረዳውም ነገር ግን ለአንዱ እንስሳ ብቻ ሥልጣኑን ሰጥቶ መሄዱ እስከ ዛሬ ድረስ ከእርሱ በታች እኩል ሆነው የኖሩትን ታማኞቹን ማባላት መስሎ ታየው፡፡ ስለዚህም ‹ሥልጣን በተርታ ሥጋ በገበታ› ብሎ ሥልጣኑን ቆራርሶ ለሁሉም በየዐቅማቸው ለማካፈል ወሰነ፡፡ በዚህም መሠረት ነበርን የጦር ሚኒስትር፣ ዝንጀሮን ዋና ዳኛ፣ ጦጣን የገንዘብ ተቆጣጣሪ፣ ቀበሮን የሥጋ ኃላፊ፣ ዝሆንን ምግብ አከፋፋይ፣ አጋዘንን የሠራተኞች ተቆጣጣሪ፣ ተኩላን ፖሊስ አድርጎ ሰየማቸው፡፡ 
    ሁሉም የጫካው እንስሳት ሹመት ሲደርሳቸው ሁለት እንስሳት ግን ምንም ሳያገኙ ቀሩ፡፡ ኤሊ እና ጥንቸል፡፡ አንበሳውም ‹‹ዔሊ እጅግ ዘገምተኛና ዛሬ ተነሥታ የዛሬ ሳምንት የምትደርስ ፍጡር ናት፡፡ ለእርሷ ሹመት መስጠት ማለት በሹመት ላይ መቀለድ ማለት ነው›› ሲል እንስሳቱ ሁሉ ሳቁ፡፡ ወደ ጥንቸልም ዞር ብሎ ‹አንቺ ሚጢጢ ፍጡር አሁን ላንቺ ሥልጣን ቢሰጥሽ ምን ታደርጊበታለሽ›› ሲል ተሳለቀባት፡፡ ይህም በእንስሳቱ ሳቅ ላይ ሌላ የሳቅ ዳረጎት ጨመረላቸው፡፡
    አንበሳውም ወደ ጉዳዩ ሄደ፡፡
    አንበሳው ከሄደ በኋላ የአንበሳን አለመኖር ያዩ የሩቅ ጎረቤቶቻቸው በእንስሳቱ ላይ ጦርነት ከፈቱባቸው፡፡ ይህ ጦርነት ከብዙ ዘመን በኋላ የተከሰተ ነበር፡፡ ነብር የጦር ሚኒስትር ሲሆን የመጀመርያው ነበርና የሚይዘውንና የሚጨብጠውን አጣ፡፡ በአንድ በኩል ወታደር ሲያሰለጥን በሌላ በኩል ሲዋጋ ጦርነቱን መቋቋም አቃተው፡፡ ምግብ አከፋፋዩም ምግቡን ከማከፋፋሉ በፊት በጠላት ተማረከበት፤ ዳኛውም ከነመንበሩ ተያዘ፡፡ ጦርነቱም እየገፋ መጥቶ መሐል ጫካው ላይ ደረሰ፡፡
    የጎረቤት አራዊት ያንን ጫካ የወረሩበት ምክንያት ወዲያው ነበር የታወቀው፡፡ እዚያ ጫካ ያሉ እንስሳት ለብዙ የችግር ዘመን የሚሆን እህል ማከማቸታቸው ይነገራል፡፡ ይህ እህል ያለበት ቦታ በካርታ ላይ ሠፍሮ በአንበሳው እጅ ነው የሚገኘው፡፡ አሁን አንበሳ ከሄደ ደግሞ ከሹመኞቹ ለአንዱ ስለሚሰጠው ጫካውን ወርሮ እህሉን መዝረፍ ነበር ዓላማቸው፡፡
    ይህ የእህሉ ካርታ በዳኝነት የተሰየመው ዝንጀሮ ጋ መኖሩ ተወርቷል፡፡ ዝንጀሮ ግን ማንበብና መጻፍ አይችልም ነበር፡፡ አንዳንድ እንስሳትም ዝንጀሮ የተሾመው በትከሻውና ለአንበሳው በዛፍ ጫፍ ላይ የሚገኝ ጣፋጭ ፍሬ እያመጣ እጅ መንሻ በመስጠቱ ነው እያሉ ያሙት ነበር፡፡ እንዲያውም ወዲያው እንደተሾመ በፈረደው ፍርድ ተከሳሹን ትቶ በስሕተት በከሳሹ ላይ እንደፈረደበት ይነገራል፡፡ ለምን እንዲህ እንዳደረገ ሲጠየቅም ‹‹ዋናው ፍርድ መሰጠቱ እንጂ በማን ላይ መፈረዱ አይደለም፤ ሪፖርት የሚቀርበውኮ ይህንን ያህል ፍርድ ተሰጠ ተብሎ እንጂ በእነ እገሌ ላይ ተፈረደ ተብሎ አይደለም›› ማለቱ ተወርቷል፡፡ በዚያም ምክንያት ‹እርሱ ዘንድ ከስሶ ከመሄድ ተከስሶ መሄድ ይሻላል› እየተባለ እስከ መነገር መድረሱን የሚናገሩ አሉ፡፡
    ዝንጀሮው ተይዞ የእህሉን ቦታ የሚያሳየውን ካርታ ሲጠየቅ ግን ካርታ መጫወት እንጂ ካርታ ማንበብ እንደማይችል ነበር በኀዘን የገለጠው፡፡ ይህንንም ቦታ ሊያገኘ የቻለው ከታላላቆች ጋር ካርታ በመጫወቱና በማንኛውም ጊዜ ተጠንቅቆ በመሸነፉ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ከታላላቆች ጋር በሚደረግ የካርታ ጨዋታ ጥንቃቄ መደረግ ያለበትም ላለመሸነፍ ሳይሆን ላለማሸነፍ መሆን እንዳለበትም መክሯል፡፡
    እርሱ ዘንድ የለም የተባለው ካርታ ምናልባት ገንዘብ ቤቷ ጦጣ ጋር ሊኖር ይችላል ተብሎ ተፈልጎ ነበር፡፡ ጦጣ ግን ልትገኝ አልቻለችም፡፡ አንዳንድ ምርኮኛ የሆኑ እንስሳትም ጦጣ ገንዘቡን ከመቆጣጠር ይልቅ ገንዘቡ ሳይቆጣጠራት እንዳልቀረ ገምተዋል፡፡ ገንዘቡንም ወደ ሌላ ጫካ ሳታዞረው እንዳልቀረች ይጠራጠራሉ፡፡ ለብዙ ዘመናት ከዚያ ጫካ ወጥታ የማታውቀው ጦጣ ሰሞኑን የውጭ ጉዞ ማብዛቷንና ከአካባቢው ጫካዎች በአንዱ ደግሞ ገንዘብ ቆጥራ ስትከፍል መታየቷ ይወራል፡፡ አሁንም የጠፋችው ወደዚያው ሄዳ ሊሆን እንደሚችል የሚገምቱ አሉ፡፡
    ዝሆኑ ስለ ካርታው የሚያውቀውም ሆነ እህል ስለ መከማቸቱ የሰማው ነገር የለም፡፡ እርሱ ስለ ጫካው አስቦ እንደማያውቅ ይነገራል፡፡ ከአንዲት ሚስቱና ከሦስት ቡችሎቹ ጋር የሚኖርባት አካባቢ አለችው፡፡ እርሱም ከዚያ አካባቢ መውጣት አይፈልግም፤ ሌላ እንስሳም ወደ አካባቢው አያስጠጋም፡፡ ለርሱ ጫካው ማለት መንደሩ ብቻ ነው፡፡ አሁንም የጎረቤት አራዊት ጫካውን ሲወርሩት እርሱ ቁብ አልሰጠውም፡፡ ለእርሱ ጦርነቱ ተጀመረ የሚለው እርሱ መንደር ጦርነቱ ሲደርስ ብቻ ነው፡፡ አንዳንዶቹን እንስሳት ያሳቀቸው ነገር ቢኖር ዝሆኑ ከጥቂት ቀናት በላይ የሚመገበው ነገር እንደሌለውና ምግቡን የሚያገኘው ከሌሎች አካባቢ መሆኑን አለመረዳቱ ነው፡፡
    ቀበሮም ቢሆን ጦርነቱ አላስጨነቀውም፡፡ እንዲያውም ከጦርነቱ እንዴት ማትረፍ እንደሚችል እያሰበ ነበር፡፡ ቀበሮ ‹አንዱ ሲሞት አንዱ ይወለዳል፤ አንዱ ሲዳር አንዱ ይሞታል› የሚባል አባባል አለው፡፡ ስለዚህም በጫካው ውስጥ አንድ ችግር ሲከሰት ችግሩን እንዴት እንደሚፈታው ማሰብ ቀበሮን አይመለከተውም፡፡ እርሱ የሚያስበው ከችግሩ እንዴት ማትረፍ እንደሚቻል ነው፡፡
    እንዲያውም አንዳንዶች የሚከተለውን ነገር ማሳያ ነው ብለው ይናገሩለታል፡፡
    አንድ ጊዜ በጫካው የሚገኘው ወንዝ ተበከለና ብዙ እንስሳት ሞቱ፡፡ ወንዙ ከሁለት አቅጣጫ መጥቶ ጫካው ድንበር ላይ ሲደርስ አንድ ይሆናል፡፡ ቀበሮም በሽታው ሳያስጨንቀው ወዲያውኑ መድኃኒት ዐዋቂ ነኝ ብሎ መድኃኒት መቸብቸብ ጀመረ፡፡ እንስሳቱ ሁሉ በሽታውን ስለፈሩት በውድ ዋጋ ያንን ያልታመነ መድኃኒት እየገዙ መውሰድ ጀመሩ፡፡
    የተመረዘው ውኃ የሚመጣው ከአንደኛው አቅጣጫ መሆኑ ሲታወቅ እንስሳቱ ሁሉ አንደኛውን ወንዝ ለመገደብ ተስማሙ፡፡ ይህንን ሃሳብ የተቃወመው ቀበሮ ብቻ ነው፡፡ ቀበሮ ‹‹ይህንን ማድረግ የአካባቢውን ሥነ ምሕዳር ይጎዳዋል፡፡ የአካባቢው ሥነ ምሕዳር ከሚጎዳ ደግሞ እኛ ብንሠዋ ይሻላል›› ሲል ሃሳብ ሰጥቷል፡፡
    አሁንም ቀበሮው በጦርነቱ የራሱ ጫካ መወረሩን ረስቶ የሞቱትን እንስሳት ሥጋ እየሰበሰበ ለጎረቤት ጫካዎች መሸጥ ጀምሯል ይባላል፡፡ ዛሬ ጠዋት ሥጋ ተሸክሞ ከጫካ ሲወጣ በወራሪዎቹ ወታደሮች ተይዞ ነበር፡፡ ‹የአህሉን ቦታ የሚያሳየው ካርታ የት ነው ያለው?›› ተብሎ ሲጠየቅ ‹‹የምን የእህል ካርታ ነው? የተከማቸ እህል መኖሩን ባውቅ እኔ ወደ ሥጋ ንግድ ውስጥ ለምን እገባ ነበር?›› ሲል ነበር መልሶ የጠየቃቸው፡፡ ወታሮቹ ከሄዱ በኋላ ቀበሮ ራሱን ረገመ፡፡ ‹‹ እንዴት ይህንን ነገር እስከ ዛሬ አልሰማሁም? ›› ሲል ተቆጨ፡፡
    የሞተው ሞቶ፣ የተሰደደው ተሰድዶ፣ የተረፉትም እየቆሰሉ በየጎሬው ተኝተው ወራሪዎቹ ጫካውን ለቅቀው ወጡ፡፡ አሁን ከባድ የሆነው እነዚያ ለጫካው ሲሉ የቆሰሉና የታመሙ ምን ይብሉ? ምን በልተው ከሕመማቸው ይዳኑ? ምን በልተው ቁስላቸውን ይጠግኑ? የተሰደዱትስ በሄዱበት ይበላሉ፡፡ የሞቱትም ዐርፈዋል፡፡ ካሉት በታች፣ ከሞቱት በላይ ሆነው የተረፉትስ?
    አንበሳው ትቶት በሄደው ጫካ የሆነውን ሰምቶ እያገሣና እየደነፋ መጣ፡፡ የነበረው እንዳልነበረ ሆኖም ጠበቀው፡፡ ብዙዎቹ ሞተዋል፤ ሌሎቹ ተሰድደዋል፤ የቀሩትም ቆስለው ተኝተዋል፡፡ በየቤቱ ለተኙትና ለሚያቃስቱት የሚላስና የሚቀመስ ግን አልነበረም፡፡ አንበሳው ወደ ዝንጀሮ ሄዶ የሰጠውን ወረቀት ጠየቀው፡፡ ዝንጀሮው ግን ወረቀቶቹን በኪሎ ከመሸጥ ባለፈ ምንም እንዳላደረጋቸው ተናገረ፡፡ አንበሳው በድንጋጤ ነበር ዐመዱ ቡን ያለው፡፡ ‹‹ለመሆኑ እነዚያ ወረቀቶች ምን ምን እንደያዙ ታውቃለህ?›› አለው፡፡ ዝንጀሮው ግን ‹‹ ጌታዬ ወረቀት መሆናቸውን ካልሆነ በቀር የማውቀው ነገር የለም፡፡ እኔኮ ዝንጀሮ ስለሆንኩና ዛፍ ጫፍ ላይ መውጣት ስለቻልኩ ብቻ ነበር የተሾምኩት፡፡›› ሲል በኀዘን ተናግሯል፡፡
    ቢታሰስ ቢታመስ ያ ወረቀት አልተገኘም፡፡ አንበሳው የሚያደርገው ጨንቆት ጎምለል ጎምለል ሲል ድንገት እግሩ ሥር አንዳች ንቅናቄ ተሰማው፡፡ አፈሩ ርግፍግፍ ይላል፡፡ አንዳች አውሬ ከምድር ሥር እየወጣ ነው ብሎ ፈራና ፈቀቅ አለ፡፡ ዓይኑንም ተከለ፡፡ ያ አፈር መሳይ ነገር ረግፎ ረግፎ ወደ ሌላ ቅርጽ ተቀየረ፡፡ ያቺ ዘገምተኛ ዔሊ ነበረች፡፡ አንበሳ ተናደደ፡፡ ‹‹ አንቺ ዘገምተኛ ፍጡር፤ ይህ ሁሉ እንስሳ ሲያልቅ አንቺ እንዴት ተረፍሽ›› አላት፡፡
    ‹‹ጌታው አይሳሳቱ ፈጣሪ የማይጠቅም ፍጡር አልፈጠረም፡፡ እያንዳንዳችን በሌላ የማይሸፈን አንዳች ቀዳዳ እንድንሞላ የተፈጠርን ነን፡፡ እያንዳንዳችን በሌላ የማይቻል አንዳች ልዩ ችሎታ አለን፡፡ ታላቅነትና ታናሽነት ሥጋን እንጂ ነፍስን አይለካም፡፡ የሥጋ እንጂ የነፍስ ታናሽ የለውም፡፡ ጌታዬ አንዳንድ ጊዜ ታላቅነትና ታናሽነት የአጋጣሚና የዕድል ጉዳይ እንጂ የችሎታ ላይሆን ይችላል፡፡ በዚህ ዓለም ዝሆኑም ትንኙም ያስፈልጋሉ፡፡ በአንድ መሥሪያ ቤት ጥበቃውም፣ መዝገብ ቤቱም፣ የጽዳት ባለሞያውም፣ አትክልተኛውም፣ ተላላኪውም የሥራ አስኪያጁንና የዳይሬክተሩን ያህል ያስፈልጋሉ፡፡ ተራ ሰዎችም የመሪዎችን ያህል ያስፈልጋሉ፡፡ እንዲያውም ዓለምን የሚያድኗትም የሚያጠፏትም ታላላቅ የተባሉ ነገሮች ሳይሆኑ ታናናሽ የተባሉ ነገሮች ናቸው፡፡
    ‹‹ያ የሚፈልጉት ካርታ የሚገኘው እኔ ዘንድ ነው፡፡ ወራሪዎቹ ሁሉንም ፈትሸዋል፡፡ እኔን ግን አልፈተሹም፡፡ ምክንያቱም አንድም ስለናቁኝ አንድም ራሴን ከመሬት ጋር ቀብሬ ተመሳስዬ ስለነበር፡፡ እኔ ድንጋይ ነበር የምመስላቸው፡፡ ነገር ግን ድንጋይ አልነበርኩም፡፡ የሚፈልጉት ነገር የሚንቁኝ እኔ ዘንድ መኖሩን መጠርጠር ግን አልቻሉም፡፡ ስለዚህ ካርታውን እርስዎ እስኪመጡ ደበቅኩት፡፡›› አንገቷን ቀስ ብላ አስግጋ ካርታውን አቀበለችው፡፡
    ‹ትገርሚያለሽ፤ ለመሆኑ አንቺን ምን ብዬ ነበር የሾምኩሽ?›› ሲል በአግራሞት ጠየቃት፡፡
    ‹‹አይ ጌታዬ እንደ እኔ ዓይነቶቹኮ ሥራውን እንጂ ሹመትና ደሞዙን አናገኘውም›› አለችው፡፡
    ‹‹አሁን ግን መሾም ያለብሽ አንቺ ነሽ›› አላት፡፡
    ‹‹የለም ጌታው እንደዚያ አይበሉ፡፡ አሁን ብዙዎች ይመጡና ያዥው ብዬ የሰጠኋት እኔ ነኝ፤ እርሷም እንዳትታይ የደበቅኳት እኔ ነኝ ብለው ዋጋውን አስከፍለውኝ ዋጋውን እንደሚወስዱ ዐውቃለሁ፡፡›› አለችው፡፡ 
    © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የተስተናገደ ነው

    Read More
    Read more

Latest Articles

Most Popular