Health and Food

 • የጀርባ ሕመም [ በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር ]

  የጀርባ ሕመም
  (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

  የጀርባ ሕመም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተሰባችን ክፍል እያጠቃ የሚገኝ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ይህ ሕመም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የተለመደ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን በወጣትነት የዕድሜ ክልል ባሉ ሰዎች ላይም እየተበራከተ ይገኛል፡፡

  ► የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል?

  የጀርባ ሕመም ከማንኛቸውም የሰው ጀርባን ከሚሰሩ የሰውንት ክፍሎች ሊነሳ ይችላል፡፡
  እነዚህም፤

  ✔ የጀርባ ጡንቻዎች መሳሳብ (መሸማቀቅ)
  ✔ ከባድ ዕቃን ያለአግባብ ለማንሳት መሞከር
  ✔ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ እንቅስቃሴ
  ✔ የዲስክ መንሸራተት 
  ✔ የመገጣጠሚያ ላይ ኢንፌክሽን
  ✔ የአጥንት መሳሳት

  ► የጀርባ ሕመም ከዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታችን ጋር ይያያዛል፡፡

  ✔ ከባድ ዕቃን በመግፋት ወይንም በመጎተት
  ✔ ከባድ ዕቃን በመሸከም ወይም በማንሳት
  ✔ ለብዙ ሰዓት በመቆም
  ✔ ለብዙ ሰዓታት አጎንብሶ መቀመጥ
  ✔ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት መኪና ማሽከርከር

  ► የጀርባ ሕመምን እንዴት መከላከል ይቻላል?

  ✔ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡- ኤሮቢክስ የሚባለውን የስፖርት ዓይነት መሥራት የሰውነታችንን አቅም ከመጨመር ባለፈ ክብደታችንን በመቀነስ የጀርባ ሕመም ይከላከላል፡፡

  ✔ ሲጋራ ማጤስን ማቆም፡- ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሲጋራን የሚያጤሱ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ለጀርባ ሕመም ተጋላጭ ናቸው፡፡

  ✔ የሰውንት ክብደት መቀነስ፡- የሰውነት ክብደታቸው የጨመረ ሰዎች የጀርባ ሕመም ይኖርባቸዋል፡፡

  ✔ የተስተካከለ አቀማመጥ፡- በምንቀመጥበት ጊዜ ጀርባችንን የሚደግፍ እና እጃችንን የምናሳርፍበት ቀጥ ያለ አቀማመጥ መያዝ፡፡

  ✔ የተስተካከለ አቋቋም፡- በምንቆምበት ጊዜ የሰውነት ክብደታችን በሁለቱም እግሮቻችን በእኩል መጠን እንዲያርፍ ማድርግ እና ቀጥ ብለን ሳንቆለመም መቆም፡፡

  ✔ ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በአግባቡ ማንሳት፡- ክብደት ያላቸውን በምናነሳበት ጊዜ ክብደቱን ከወገባችን/ከጀርባችን ይልቅ በእግሮቻችን ላይ እንዲያርፍ ማድርግ ተገቢ ነው፡፡ ዕቃዎችን በምናንቀሳቅስበት ጊዜ ከመጎተት ይልቅ መግፋትተመራጭ ነው፡፡

  ✔ ጫማ፡- የጀርባ ሕመም እንዳይሰማን የምንጫማቸው ጫማዎች ምቹ ሊሆኑ ይገባል፡፡

  ✔ መኪና በምንሽከረክርበት ወቅት ጀርባችንን መደገፍ፡፡ ለረጅም ሰዓት የምናሽከረክር ከሆነ በየማሃሉ ከመኪና በመውረድ ሰውነትን ማንሳሰቀስና ዕረፍት መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

  ✔ የአልጋ ፍራሽ ምቾት፡- የምንተኛበት የአልጋ ፍራሽ ቀጥ ያለ መሆን አለበት፡፡ 

  የጀርባ ሕመም ከባድ የሆኑ የጤና ችግሮች ምልክት ሊሆን ስለሚችል በቀላሉ ሊመለከቱት አይገባም፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የሚጠቀሱት ተጫማሪ ምልክቶች ካሉ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡እነዚህም፤

  ✔ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ወይንም መውደቅን ተከትሎ የመጣ የጀርባ ሕመም
  ✔ ከወር በላይ የቆየ እና እየባሰ የመጣ የጀርባ ሕመም 
  ✔ በሕመም ማስታገሻ እና ዕረፍት በመውሰድ ለውጥ የማያመጣ የጀርባ ሕመም
  ✔ ከወገብ በታች የመደንዘዝ ስሜት
  ✔ ደም የቀላቀለ ሽንት መኖር
  ✔ ከፍተኛ ትኩሳት መኖር እና ሆድ ሕመም መሰማት ናቸው፡፡

  በቤቶ ሆነው ሊያከናውኑት የሚችሉትን ይህን ቀላል የ አካል ብቃት እንቅስቃሴ በዚህ አድራሻ ማግኘት ይችላሉ። [ http://honeliat.com/?p=471 ]  ጤና ይስጥልኝ

  Read More
  Read more
 • 15 Health Benefits of Eating Apples

  In 2004, USDA scientists investigated over 100 foods to measure their antioxidant concentration per serving size. Two apples—Red Delicious and Granny Smith—ranked 12th and 13th respectively. Antioxidants are disease-fighting compounds. Scientists believe these compounds help prevent and repair oxidation damage that happens during normal cell activity. Apples are also full of a fibre called pectin—a medium-sized apple contains about 4 grams of fibre. Pectin is classed as a soluble, fermentable and viscous fibre, a combination that gives it a huge list of health benefits. 

   

  Read More
  Read more
 • ዘይቱን ለጤና ያለው ጥቅም

  እንደዘበት በፍራፍሬ ጭማቂ ቤቶች ገብተን የምንጠቀመው ዘይቱን ከፍተኛ የሆነ የጤና ጠቀሜታ ባላቸው ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ነው። የዘይቱን ፍሬ በአውሮፓ ፣ እስያ እና በደቡብ አሜሪካ አገራት በስፋት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ፥ በአገራችንም በጥሬው አልያም በተለያዩ ጥማቂ ቤቶች በተለያየ አቀራረብ ጥቅም ላይ ይውላል።

  zeyetun
  የዘይቱን ፍሬ በቫይታሚን ኤ ፣ ሲ ፣ በፖታሺየም ፣ ኮፐር ፣ ፕሮቲንና በሌሎች ለሰውነታችን ከፍተኛ ጥቅም በሚሰጡ ንጥረ ነገሮች የተሞላ ነው። አንድ የዘይቱን ፍሬ በመመገብ ከአንድ ብርቱካን የምናገኘውን ቫይታሚን በአራት እጥፍ ማሳደግ ይቻላል። ለምሳሌ አንድ ሰው 100 ግራም ዘይቱን ቢመገብ ወይም በጭማቂ መልክ ቢጠጣ በግራም 43.2 ካርቦሀይድሬት ፣ 8.92 ስኳር ፣ 255 ፕሮቲን የሚያገኝ ሲሆን ፥ በተጨማሪ ካልሲየም ፣ አይረንና ከእንውስሳት የምናገኘውን ስብ እናገኝበታለን።
  በሌላው ዓለም ከዘይቱን ፍሬ በተጨማሪ ግንድ እና ቅጠሉ ሳይቀር ጥቅም ላይ ይውላል ፤ ለምሳሌ አሜሪካውያን የዘይቱንን ግንድ ቆንጆ ጣእም ያለው ጥብስ ለማዘጋጀት ይጠቀሙበታል። በቀደምት ግዜያትም የዘይቱን ቅጠል ለህክምና ምርምሮች ውጭት ባስገኘ መልኩ ጥቅም ላይ የዋለ እና በምርምሩም ለካንሰር እንዲሁም ለተለያዩ የባክቴሪያ ጸር መሆኑም የተረጋገጠ ሲሆን ፥ ከዘይቱ ቅጠል የሚዘጋጀው የምግብ ዘይትም የካንሰርን ዕድግት ለመግታት ጥቅም ይሰጣል። እርስዎስ ይህን ዘርፈ ብዜ ጥቅም ያለው የፍራፍሬ ዝርያ በምን መልኩ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ?
  ምንጭ -አዲስ አድማስ

  Read More
  Read more
 • ውሀና ጠቀሜታዎቹ

  ከመተኛትዎ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡ ስትሮክን እና የልብ ህመምን ለመከላከል ይረዳዎታልና 
  ጠዋት ከእንቅልፍዎ እንደተነሱ 2 ብርጭቆ ውሃ ከጠጡ ውስጣዊ የሰውነት አካላትዎን ለማነቃቃት ያግዝዎታል፡፡ 
  ሻወር ከመውሰድዎ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ የሚጠጡ ከሆነ ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመከላከል ይጠቅሞታል፡፡ 
  ከምግብ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ለምግብ መንሸራሸር ይረዳል 
  ምግብ ከመመገብዎ 30 ደቂቃ በፊት በቂ ውሃ ይጠጡ፡፡ ብዙ ባለመመገብ የሰውነት ክብደትዎን ለመቀነስ እንዲችሉ ያግዞታል፡፡

  Read More
  Read more
 • ስለ አራቱ የድንግልና ዓይነቶች ምን ያህል ያውቃሉ?

  ከሊሊ ሞገስ

  በዚህ ጉዳይ ላይ ሴቶችን ለይተን ተጠያቂ ማድረጋችን የድርጊት ተቀባይ በመሆናቸውና ውጤት የአስተናጋጅነት እጣ ፈንታው በእነሱ በኩል እንዲያመዝን ተፈጥሮ ያደላችበት ፍርጃ ስላለ ነው፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያው የግንኙነት ወቅት የአካል መጉደል የሚከናወነው በእነሱ አካል ላይ ስለሆነ ማለት ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ለድርጊቱ ሴቶች ከወንዶች የተሻለ ትውስታና የጠለቀ ስሜት ስለሚኖራቸውም ነው፡፡ ድንግልና እና ክብረንፅህና ድንግልና፡- የወንዶችም ሆነ የሴቶችን የአካል መቆጠብ ለመግለፅ የምንጠቀምበት ቃል ሲሆን ይሄም የሚያገለግለው ከግብረ ስጋ ግንኙነት መቆጠብን ይመሰክራል፡፡ ይህ የመቆጠብና የመጠበቅ ሒደትም ለሰውነቴ ክብር መስጠት ነውና የሰውነትን ንፅህና ለመግለፅ ስንጠቀምበት ክብረ ንፅህና (የንፅህና ክብር) በማለት ይብራራል፡፡ ድንግልና በምን ይገለፃል? በእርግጥ ለሁለቱም ፆታ መታቀብን ተከትሎ ቢያገለግልም በወንዶች ላይ መታቀቡና መጽናቱን ተከትሎ የሚታይ አካላዊ ለውጥ የለም፡፡ በሴቶች በኩል ግን የተራክቦ አካላት ከሆኑት መሀል በብልት አካባቢ ይህን የድንግልና መገለጫ ምልክት ይሆን ዘንድ ተፈጥሮ አስቀምጦት ይገኛል፡፡ በምን መልኩ? ድንግልና በሴቶች ብልት በራፍ ላይ የተቀመጠ አነስተኛ መጠን ያለው በደም ስሮች የተሞላ ስስና ሴንሴቲቭ /ስሱ/ የሆነ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ይህ ስስ የሰውነት አካል ለሽንትና ለወር አበባ መፍሰሻ በሚያገለግል መልኩ በትንሿ ጣት ልክ ክፍተት ያለው ክብ ቀዳዳ ነው፡፡ የድንግልና አይነት የድንግልና አይነት በተለያዩ ሴቶች ላይ በአራት (4) ሁኔታ ይገኛል፡፡ 1ኛ/ ሙሉ የብልት አካልን በራፍ እንደ መጋረጃ የዘጋና ለወር አበባና ለሽንት ማለፊያ በትንሿ ጣት ልክ ቀዳዳ በክብነት ያለው ሆኖ ይገኛል፡፡ 2ኛ/ ብዙ ጊዜ ባይሆንም በአንዳንድ ሴቶች ላይ እንደሚታየው የወንፊት መልክ በያዘ የተበሳሳ በርካታ ቀዳዳዎች ሙሉ ለሙሉ የብልቱ በራፍ የተጋረደ ሆኖ የሚገኝበት ሁኔታ ነው፡፡ 3ኛ/ በተፈጥሮ ምንም አይነት የሰውነት ክፍል በብልቱ በራፍ ላይ ሳይጋረድ ወይም የብልቱ በራፍ ከሆነው ቀዳዳ በላይ በሆነ አካል ግርዶሽ ተሸፍኖ የሚገኝበት አጋጣሚም አለ፡፡ እነዚህ በተፈጥሮ የሚሆኑ ሲሆኑ በግንኙነት ጊዜ በሚፈጠረው ፍትጊያና በወንዱ አካል (ብልት) የሚወገዱ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ በ4ኛ/ ደረጃ የሚጠቀሰው ድንግልናው በተፈጥሮ በጠነከረ ቆዳና በቀላሉ በወንዱ አካል (ብልት) ሊወገድ የማይችል አይነት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ድንግልና ብዙ ጊዜ በህክምና ተቋም በመሄድ በቀዶ ህክምና ከሴቷ ብልት በራፍ የሚወገድ ለተራክቦ አካሏ የሚስተካከልበት ሁኔታ ነው፡፡ ከሞላ ጎደል የሴት ልጆች ድንግልና በዚሁ መልኩ በተፈጥሮ የሚሰጣቸው ልዩ ፀጋ ነው፡፡ ይህ ፀጋ ደግሞ አንዴ በመወለድ የሚገኝ የአንድ ጊዜ ዕድል ነውና በህይወታቸው ውስጥ ሴቶች የማይረሱት አሻራን ያነጥቡ ዘንድ ሰፊ ዕድል ያረገዘ ነው፡፡ ይህ አካልና የክብር መግለጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረግ የግብረስጋ ግንኙነት ሊጠፋ ይችላል፡፡ እንዲሁም በአላስፈላጊ እንቅስቃሴም፣ በፈረስና ሳይክል ግልቢያ፣ ከባድ ዕቃ በማንሳትና በጀርባ በመሸከም በሂደት በመስፋትም ሆነ በመተርተር ሊጠፋ ይችላል፡፡ ግብረስጋ ግንኙነት ምንድነው? የግብረስጋ ግንኙነት ማለት ወንድና ሴት የሆኑ ፆታዎች በተራክቦ አካላት የሚፈፅሙት የአካል መገናኘት ግብረ ስጋ ግንኙነት ሲባል ሂደቱ ግን የተለያዩ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ስሜቶችን ይዞ ይገኛል፡፡ ይህ ቢሆንም አላማው ግን አንድም ስሜት (ስጋዊ ፍላጎትን) ለማርካትና ምላሽ ለመስጠት ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የግብረ ስጋ ግንኙነት ትርጉም ዘር ለመተካት የሚያደርግ ሂደት በመሆን ይገለፃል፡፡ ከዚህ አኳያ ሴቶች ወንዶች አካላዊ በሆነ ንክኪ ስሜታቸውን ምላሽ ለመስጠትም ሆነ ዘር ለመተካት በሚደረግ ግንኙነት ይህን አካል ያጡታል፡፡ ይህ ደግሞ ፈቅደውና ተገደው የሚሆንበት አጋጣሚ እጅጉን ሰፊ ነው፡፡ ፈቅደውም ሆነ ተገደው ክብረ ንፅህናቸውን በማጣትም ሆነ በተለያየ መልኩ ካጡት በኋላ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባለው የግብረ ስጋ ግንኙነት ሴቶች ምን ስሜት ይሰማቸዋል? የሚለው አብይ ጉዳያችን ነው፡፡ ለምን? የትውልድ መሸጋገሪያዎች ሴቶች እናቶች ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ሴቶች የህብረተሰቡ ግማሽ አካል ናቸው፡፡ እውነቱ ይሄ ከሆነ የሴቶች ጤናማነት ያለው አስተሳሰብ ጤናማ ትውልድን በመቅረጽ ጥሩ ዜጋን ለመተካት ይረዳልና ያለፈውን ለማረም፣ ለሚመጣው ትውልድም ከሚፈጥረው ስሜት አኳያ ተሞክሮን በማኖር መማማሪያ ለማትረፍ ከሚል በመነሳት ነው ይህን ሀሳብ የያዘ ደብዳቤ በየቦታው ለሴት እህቶቻችን በመስጠት የሰጡንን የስሜት ነፀብራቅ ለማቅረብ የወሰነው፡፡ ፍቅር እና ሴክስ ምንድናቸው? ፍቅርና ሴክስ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ያህል ግድ ናቸው የሚባልበት በአራት ነጥብ የተዘጋ ገለፃ የለም፡፡ ሁለትም አንድም ናቸው፡፡ ሁለትነታቸው በአተረጓጎም የሚለያዩና የተራራቁ ሲሆኑ፣ አንድነታቸው ግን ከመፈቃቀድ በኋላ አንዳቸው ለአንዳቸው መደራጀትና መጠናከር ጠንካራ አስተዋፅኦ መስጠታቸው ነው፡፡ ፍቅር ኖሮ ሴክስ ሲታከልበት ይበልጥ መግባባት ይቻላል፡፡ ፍቅር ባይኖርም በሴክስ መግባባት ሲቻል ያ መግባባት አንዱ የፍቅር ግብአት በመሆን ፍቅርን ለመፍጠር ይቻላል፡፡ በዋናነት ግን አሳማኝ በሆኑ ምክንያቶች ሲፈተሽ ፍቅር ላቅ ብሎ ይገኛል፡፡ ፍቅር መስዋዕትነት አንዱ ባህሪው ነውና በሴክስ ብቃት ባይደገፍም እንኳ ብቻውን ሊፀና ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ በአንፃሩ ፍቅር ሳይኖርም አካላዊ ምላሽ በመስጠት መንፈሳዊ እርካታ ባይገኝበትም ዘር ለመተካት በሚል በስጋዊ ምላሽ… እየተተረጎመ ሲኖር ይታያል፡፡ እስቲ የአንዷን አስተያየት እናንብብ፡፡ በመጀመሪያው ሴክሴ ፈሪ ሆኜ ቀርቻለሁ! ይህን ያለችን ሴት የ38 ዓመት ስትሆን 3 ልጆች አሏት፡፡ በተሟላ ትዳር ውስጥ ናት፡፡ የምትወደው ባልም አላት፡፡ እንዲህ ነበር ስሜቷን ያሰፈረችው፡፡ ‹‹…የ18 ዓመት ልጅ እያለሁ… በሰፈራችን ውስጥ ያለ ሸበላ ወጣት ጋር ፍቅር ጀመርን፡፡ ሁለታችንም ተማሪዎች ስለነበርን ከአለማችን በፊትና

  Read More
  Read more

Latest Articles

Most Popular