የሰሞኑ ወሬና ዜና የሰሜን ኮሪያ የኒኩሊየር ጥቃት ስጋት ነው። ባለፈው ሳምንት ይፋ እንደሆነው የአሜሪካውያኑ የስለላ አካላት አዲስ ግኝት ከሆነ፣ ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ ሚሳይል ላይ ተገጥሞ ለጥቃት መዋል የሚችል የኒኩሊየር መሳሪያ እየሰራች መሆኑን አረጋግጠዋል። ታዲያ ፈጽሞ አይበለውና ይህ ስጋት እውን ከሆነ የማይፈለገውን የ3ኛው የዓለም ጦርነትን ያስከትል ይሆን የሚል ስጋት አሳድሯል። ለመሆኑ የኒኩሊየር ቴክኖሎጂና የኒኩሊየር ጦር መሳሪያ ምንድነው? ታሪካዊ አመጣጡስ? እንዴትስ ነው የሚሰራው? ቢፈነዳስ የሚያሰትለው ታላቅ ጉዳት ምንድነው? ስለዚህ ጉዳይ የማስቃኘውን የምዕራፍ 11 የመዝጊያ ፕሮግራም እነሆ!
Recent news has been revolving around North Korea's possible nuclear weapon attack. According to the US intelligence community's report from last week, North Korea is making cross continental missile-ready nuclear warheads! This is perhaps one of the scariest developments that put the whole world in a potential nuclear "3rd world" war threat! What are nuclear technology and nuclear weapon? What is its historical background? How does it work? If explored what catastrophic effect will it cause? Enjoy my Season 11 finale!