ዘይቱን ለጤና ያለው ጥቅም

እንደዘበት በፍራፍሬ ጭማቂ ቤቶች ገብተን የምንጠቀመው ዘይቱን ከፍተኛ የሆነ የጤና ጠቀሜታ ባላቸው ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ነው። የዘይቱን ፍሬ በአውሮፓ ፣ እስያ እና በደቡብ አሜሪካ አገራት በስፋት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ፥ በአገራችንም በጥሬው አልያም በተለያዩ ጥማቂ ቤቶች በተለያየ አቀራረብ ጥቅም ላይ ይውላል።

zeyetun
የዘይቱን ፍሬ በቫይታሚን ኤ ፣ ሲ ፣ በፖታሺየም ፣ ኮፐር ፣ ፕሮቲንና በሌሎች ለሰውነታችን ከፍተኛ ጥቅም በሚሰጡ ንጥረ ነገሮች የተሞላ ነው። አንድ የዘይቱን ፍሬ በመመገብ ከአንድ ብርቱካን የምናገኘውን ቫይታሚን በአራት እጥፍ ማሳደግ ይቻላል። ለምሳሌ አንድ ሰው 100 ግራም ዘይቱን ቢመገብ ወይም በጭማቂ መልክ ቢጠጣ በግራም 43.2 ካርቦሀይድሬት ፣ 8.92 ስኳር ፣ 255 ፕሮቲን የሚያገኝ ሲሆን ፥ በተጨማሪ ካልሲየም ፣ አይረንና ከእንውስሳት የምናገኘውን ስብ እናገኝበታለን።
በሌላው ዓለም ከዘይቱን ፍሬ በተጨማሪ ግንድ እና ቅጠሉ ሳይቀር ጥቅም ላይ ይውላል ፤ ለምሳሌ አሜሪካውያን የዘይቱንን ግንድ ቆንጆ ጣእም ያለው ጥብስ ለማዘጋጀት ይጠቀሙበታል። በቀደምት ግዜያትም የዘይቱን ቅጠል ለህክምና ምርምሮች ውጭት ባስገኘ መልኩ ጥቅም ላይ የዋለ እና በምርምሩም ለካንሰር እንዲሁም ለተለያዩ የባክቴሪያ ጸር መሆኑም የተረጋገጠ ሲሆን ፥ ከዘይቱ ቅጠል የሚዘጋጀው የምግብ ዘይትም የካንሰርን ዕድግት ለመግታት ጥቅም ይሰጣል። እርስዎስ ይህን ዘርፈ ብዜ ጥቅም ያለው የፍራፍሬ ዝርያ በምን መልኩ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ?
ምንጭ -አዲስ አድማስ

Read More
Be the first to comment

Related Articles

  • ስለ አራቱ የድንግልና ዓይነቶች ምን ያህል ያውቃሉ?
    ስለ አራቱ የድንግልና ዓይነቶች ምን ያህል ያውቃሉ?
    ከሊሊ ሞገስ በዚህ ጉዳይ ላይ ሴቶችን ለይተን ተጠያቂ ማድረጋችን የድርጊት ተቀባይ በመሆናቸውና ውጤት የአስተናጋጅነት እጣ ፈንታው በእነሱ በኩል እንዲያመዝን ተፈጥሮ ያደላችበት ፍርጃ ስላለ ነው፡፡...
  • 15 Health Benefits of Eating Apples
    15 Health Benefits of Eating Apples
    In 2004, USDA scientists investigated over 100 foods to measure their antioxidant concentration per serving size. Two...
  • የጀርባ ሕመም [ በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር ]
    የጀርባ ሕመም [ በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር ]
    የጀርባ ሕመም(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)የጀርባ ሕመም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተሰባችን ክፍል እያጠቃ የሚገኝ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ይህ ሕመም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ...

Latest Articles

Most Popular