ውቢት ኢትዮጵያ!

 

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን “የ13 ወር ፀጋ” በሚል ርዕስ ከሚያሳትማቸው ፖስተሮች የዝነኛዋ “ውቢት ኢትዮጵያ” አስደናቂ ተፈጥሮአዊ ውበትና ግርማ ሞገስ የታየበት ፖስተርዋ ሁሌ ከማይረሱን መሃል አንዳቸው ነው።

የ4 ልጆች እናት የነበረችው ውቢት አመንሲሳ በወለጋ ክፍለ ሀገር ተወልዳ አድጋ ወደ አዲስ አበባ ተጉዛ እቴጌ መነን ትምህርት ቤት ተምራ ቦኋላ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን ተቀጥራ ለመስራት አበቃች። ከልጆችዋና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀጥረው ይሰሩ ከነበረው ባለቤቷ ጋር አዲስ አበባ ትኖር ነበር። ከዚህ ቀደም የውቢት አመንሲሳ እውነተኛ ስሟ አልማዝ አመንሲሳ ነው ብለን ተናግረን ነበር፡ የተሳሳተ መረጃ በመልቀቃችን ይቅርታችሁን እንጠይቃለን። በቅርቡ እንደተረዳነው ግን አልማዝ አመንሲሳ በወቅቱ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩና ዛሬ ነዋሪነታቸው አሜሪካ የሆነው የውቢት ኢትዮጵያ እህት ናቸው። ከአልማዝ ጋር አብረው ይሰሩ የነበሩት የስራ ባልደረባቸው ልንረዳው እንደቻልነው ምስሉ ላይ ያለችው የአልማዝ እህት ውቢት አመንሲሳ ከቱሪዝም ስራዋ ውጭ ሞዴል ወይ የፊልም ተዋናይት አልነበረችም። 1970ዎቹ የብሄራዊ ቱሪዝም ኮሚሽን ለገቢ ማሰባሰብያ የሚሆኑ ድንቅ ድንቅ ፎቶዎችን አንስቶ ለመልቀቅ የፈለገበት ወቅት ነበር። ውቢት በቱሪዝም ኮሚሽን ፎቶ የመነሳት እድል አጋጥሟት ነው ለ <<ውቢት ኢትዮጵያ>>ነቷ ልታበቃ የቻለችው። ኩባዊ ኢትዮጵያዊው የታሪክ ምሁር ኤድዋርዶ ባይሮኖ እንዳስረዳን ውቢት አመንሲሳ ለፎቶዉ 5 ሳንቲም ሳትቀበል ፎቶዉ ያስገኘና እስከ ዛሬ እያመነጨ ያለው ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለኮሚሽኑ እንዲረከብና የሃገራችን ቱሪዝምን እንዲያገለግል ፍላጎቷ ነበር።

በ2000 ዓም ለህክምና ወደ አሜሪካ አምርታ ህዳር ወር 2001 ዓም ውቢት ኢትዮጵያ በሞት ተለየችን።

መልከ መልካሟ ውቢት ኢትዮጵያ ሀገርዋን ላገለገለችበትና ስማችን ላስጠራችበት ምስጋናችን ይገባታል።

ነፍስሽን በገነት ያኑረው <3 

This is the famous image of "Woubit Ethiopia" as she was dubbed. This image was taken sometime in the late seventies by Ethiopia's tourist commission board. Not much is known about the woman subject of the photo.

Her name is Woubit Amensisa. Hailing from Ethiopia's Wollega region, she later moved to Addis Ababa and was a student at Etege Menen School, before finishing her studies and getting a job with Ethiopia's tourism commission. She lived in Addis Ababa with her husband, who worked at Ethiopian Airlines, and her four children. A while ago we released this picture saying that her real name was Almaz Amensisa. We'd like to apologize for the error. The truth is, the beautiful woman in the picture is really named Woubit Amensisa, while Almaz Amensisa is her sister who worked for Ethiopian Television and now resides in the USA. Unlike what is widely believed, outside of her job at the national tourism commission, Woubit was neither a model nor an actress. Her colleagues at the national tourism office managed to convince her to take up a photo shoot opportunity at a time when the national tourism commission was collecting images to serve for promotional purposes. But her image became an international sensation. According to Cuban Ethiopian historian Eduardo Byrono, Woubit never asked for compensation for the photo and only wished that the income serve Ethiopia's tourism industry.

In 2007, Woubit came to the USA to get treatment for an undisclosed illness. Sadly, in November of 2008, Woubit Ethiopia's health had declined and she passed away in the USA.

Although every Ethiopian is familiar with the class, elegance and natural beauty she exhibits in this image, she didn't get the recognition she deserved in her lifetime.

<3 Woubit Amensisa aka Woubit Ethiopia <3 , rest in eternal peace!

To enlighten your fellow Ethiopian or anyone for that matter, like and share this pic!

Be the first to comment

Related Articles

  • የወሎ ‹‹ላሊበላ›› ትንሣኤ
    የወሎ ‹‹ላሊበላ›› ትንሣኤ
    በጥቂቱም ቢሆን ዕድሜ እየተጫጫናቸው መምጣቱ ከፊታቸውና ከመላ ሰውነታቸው ይነበባል፡፡ በተለይም ጣታቸው፣ እጃቸው፣ ክንዳቸውና ቀሪ ሰውነታቸው ጠንከርከር የሚለው መድረክ ላይ ወጥተው ማሲንቋቸውን ሲይዙ...
  • Billboard Music Awards
    Billboard Music Awards
    Nicki Minaj arrives for the 2014 Billboard Music Awards at the MGM Grand Garden Arena on May 18, 2014, in Las Vegas, Nevada....
  • How to Be a Good Wife
    How to Be a Good Wife
    Being a good wife is not easy, even if you have a near-perfect husband. To be a good wife, you have to be able to communicate...
  • Ancient city uncovered in Ethiopia | BBC News
    Ancient city uncovered in Ethiopia | BBC News
    Ancient city uncovered in Ethiopia Farmers in the eastern Ethiopian city of Harlaa have long found strange objects on their...

Latest Articles

Most Popular