Entertainment  | Mutimedia | Educational
Welcome
Login / Register

ዘይቱን ለጤና ያለው ጥቅም

እንደዘበት በፍራፍሬ ጭማቂ ቤቶች ገብተን የምንጠቀመው ዘይቱን ከፍተኛ የሆነ የጤና ጠቀሜታ ባላቸው ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ነው። የዘይቱን ፍሬ በአውሮፓ ፣ እስያ እና በደቡብ አሜሪካ አገራት በስፋት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ፥ በአገራችንም በጥሬው አልያም በተለያዩ ጥማቂ ቤቶች በተለያየ አቀራረብ ጥቅም ላይ ይውላል።

zeyetun
የዘይቱን ፍሬ በቫይታሚን ኤ ፣ ሲ ፣ በፖታሺየም ፣ ኮፐር ፣ ፕሮቲንና በሌሎች ለሰውነታችን ከፍተኛ ጥቅም በሚሰጡ ንጥረ ነገሮች የተሞላ ነው። አንድ የዘይቱን ፍሬ በመመገብ ከአንድ ብርቱካን የምናገኘውን ቫይታሚን በአራት እጥፍ ማሳደግ ይቻላል። ለምሳሌ አንድ ሰው 100 ግራም ዘይቱን ቢመገብ ወይም በጭማቂ መልክ ቢጠጣ በግራም 43.2 ካርቦሀይድሬት ፣ 8.92 ስኳር ፣ 255 ፕሮቲን የሚያገኝ ሲሆን ፥ በተጨማሪ ካልሲየም ፣ አይረንና ከእንውስሳት የምናገኘውን ስብ እናገኝበታለን።
በሌላው ዓለም ከዘይቱን ፍሬ በተጨማሪ ግንድ እና ቅጠሉ ሳይቀር ጥቅም ላይ ይውላል ፤ ለምሳሌ አሜሪካውያን የዘይቱንን ግንድ ቆንጆ ጣእም ያለው ጥብስ ለማዘጋጀት ይጠቀሙበታል። በቀደምት ግዜያትም የዘይቱን ቅጠል ለህክምና ምርምሮች ውጭት ባስገኘ መልኩ ጥቅም ላይ የዋለ እና በምርምሩም ለካንሰር እንዲሁም ለተለያዩ የባክቴሪያ ጸር መሆኑም የተረጋገጠ ሲሆን ፥ ከዘይቱ ቅጠል የሚዘጋጀው የምግብ ዘይትም የካንሰርን ዕድግት ለመግታት ጥቅም ይሰጣል። እርስዎስ ይህን ዘርፈ ብዜ ጥቅም ያለው የፍራፍሬ ዝርያ በምን መልኩ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ?
ምንጭ -አዲስ አድማስ

Read More

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles

RSS