Entertainment  | Mutimedia | Educational
Welcome
Login / Register

ተስፋና ሥጋት ያንዣበበበት የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት

እንደ አገር ከተመሠረተች ገና አራት ዓመት እንኳን ያልሞላት ደቡብ ሱዳን ከአምስት ወራት በፊት በተነሳ የእርስ በርስ ጦርነት ሳቢያ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ዜጐቿ ለስደት ሲዳረጉ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ በእርስ በርስ ግጭቱ ጦስ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

የግጭቱን መንስዔ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በቀድሞው የአገሪቷ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሪክ ማቻር የተቃጣ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ነው በማለት የሚገልጹ ሲሆን፣ የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ግን የምን መፈንቅለ መንግሥት? በማለት ይጠይቃሉ፡፡ 

በአካባቢው ያሉ አገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ በተናጠልና በኢጋድ አማካይነት የተፈጠረውን ቀውስ በእንጭጩ ለመቅጨት ያደረጉት ጥረት ፍሬ ሳያፈራ ብልጭ ድርግም እያለ እስካለፈው ዓርብ ድረስ ያስመዘገበው ውጤት አልነበረም፡፡ 

ባለፈው ዓርብ ግንቦት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ግን የኢጋድ አደራዳሪ ቡድኖችና የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማት ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ሁለቱ ወገኖች ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ከአምስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው ከመደራደራቸውም ባሻገር፣ ለአምስት ወራት የዘለቀውን ግጭት ያስቆማል የተባለ የሰላም ስምምነትም ፈርመዋል፡፡ 

ነገር ግን ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊን፣ የሌሎች አገሮችን ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የደቡብ ሱዳን መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይን፣ እንዲሁም የአማፅያኑ ቃል አቀባይን በመጥቀስ የሰላም ስምምነቱ ፊርማ ሳይደርቅና ሃያ አራት ሰዓታት እንኳን ሳይሞላው ሁለቱ ወገኖች ተመልሰው ወደ ጦርነት መግባታቸውን እየዘገቡ ነው፡፡

የስምምነቱ ይዘት

የኢጋድ ልዩ ልዑክ በመሆን ሁለቱን ወገኖች ለወራት ሲያደራድሩ በነበሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአሁኑ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ሥዩም መስፍን የተነበበው የሰላም ስምምነቱ በዋነኛነት ያካተተው፣ በ24 ሰዓት ውስጥ ተፈጻሚ የሚሆን የተኩስ ማቆም ስምምነት፣ የጥላቻ ንግግሮችን ማስወገድ፣ ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅቶች ሥራቸውን ለማቀላጠፍ የሚረዳ መተላለፊያ መፍቀድ፣ የሽግግር መንግሥት ለማቋቋም የሚረዱ ሥራዎችን መሥራትና የተሠሩትን ሥራዎች ለመገምገም ሁለቱ መሪዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ዳግም እንዲገናኙ ማድረግ የሚሉ ይገኙበታል፡፡ 

በሰላም ስምምነቱ ወቅት ሁለቱ መሪዎች በስምምነቱ ተግባራዊነት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ቢያረጋግጡም፣ ከስምምነቱ መፈረም በኋላ ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች ግን ሁለቱም ወገኖች ቃል የገቡለትን ስምምነት በማፍረስ ተመልሰው ወደ ጦርነት መግባታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ 

Read More

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles

RSS