Entertainment  | Mutimedia | Educational
Welcome
Login / Register

ሚሸል ኦባማ ከናይጀሪያ ሴቶች ጋር እንደሚቆሙ አስታወቁ

ናይጀሪያ ውስጥ ቦኮ ሃራም በሚባለው ፅንፈኛ ቡድን የተጠለፉ ወደ 300 የሚጠጉ ልጃገረዶችን ለመፈለግ ለሚደረገው ዓለምአቀፍ ጥረት ድጋፍ ለመስጠት የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳሚት እመቤት ሚሼል ኦባማ ሃሽታግ ብሪንግ ባክ አወር ገርልስ (#BringBackOurGirls) - ልጆቻችንን መልሱ የሚል መልዕክት ይዘው የተነሱትን ፎቶግራፍ ትናንት በትዊተር ለቅቀዋል፡፡

የናይጀሪያ ሴቶች የሴቶች መብቶች ጉዳይ ነው ብለው በሚያምኑት በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ሚስ ኦባማ ያደረጉትና ከጎናቸውም መቆማቸው ልባቸውን የነካው መሆኑን እየገለፁ ነው፡፡

አንዳንድ የፀጥታ ተንታኞች ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ በጉዳዩ ውስጥ መግባት ከሚኖረው ፋይዳ ይልቅ ጉዳቱ ሊያይል ይችላል የሚል ሥጋት እያሰሙ ነው፡፡

Read More

Post your comment

Comments

Be the first to comment

Related Articles

RSS